Fana: At a Speed of Life!

በቻይና በደረሰ የርዕደ መሬት አደጋ የነፍስ አድን ሥራው አሁንም እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ቻይና ቲቤት ግዛት በትናትናው ዕለት በተከሰተ ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር 126 ሲደርስ 188 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡

በዚህ አደጋ በሂማሊያ ሰሜናዊ ተዳፋት አካባቢ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች መፍረሳቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ከ30 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደሌላ ስፍራ መወሰዳቸውም ነው የተገለጸው፡፡

407 ሰዎች እስከአሁን በተደረገ ርብርበ ከአደጋው ሊተርፉ መቻላቸው ተነግሯል፡፡

በትናትናው ዕለት መጠነ ሰፊ የነፍስ አድን ሥራ እንዲደረግ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ማዘዛቸው የሚታወስ ሲሆን፥ የነፍስ አድን ስራው አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ዥኑዋ ዘግቧል፡፡

ርዕደ መሬቱ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ጥልቀት እንዳለውና ሺጋትሲ በተባለችው የቲቤት አካባቢ ሌሊት 7 ሠዓት ገደማ የተከሰተ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.