Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል በ41 ማዕከላት የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ በክልል በ41 ቋሚና ተንቀሳቃሽ ማዕከላት ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እየተከናወነ መሆኑን በኢትዮ-ቴሌኮም የሰሜን ሪጅን አስታወቀ።

በኢትዮ-ቴሌኮም የሰሜን ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ሙሉ ወልደስላሴ÷ ዲስትሪክቱ ባለፉት 8 ወራት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን ጨምሮ የዲጂታል መታወቂያ ሕትመት አገልግሎትን በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሰሜን ሪጅን ዲስትሪክት በ26 ቋሚና 15 ተንቀሳቃሽ ማዕከላት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ደንበኞች የኩባንያውን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ማዕከላት ሲያመሩ ብሎም በተንቀሳቃሽ ማዕከላት ባሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎቱን እንዲያገኙ በመደረግ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዲስትሪክቱ እስካሁን ከ235 ሺህ በላይ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው÷ በቀጣይ ማዕከላቱን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

ሕብረተሰቡ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያለውን ጠቀሜታ እንዲረዱ የግንዛቤ ማስጨበጭ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ነው ያመላከቱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.