ማንቼስተር ዩናይትድ ሲሸነፍ ቼልሲ ነጥብ ጣለ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መረሐ ግብር ኦልድትራፎርድ ላይ ቦርንሞውዝን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 ሲሸነፍ ቼልሲ በኤቨርተን ነጥብ ጥሏል፡፡
አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ለቦርንሞውዝ የማሸነፊያ ግቦችን ዲያን ሁጅሰን፣ ክሉቨርት እና ሴሜኞ አስቆጥረዋል፡፡
ወደ ጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም ያቀናው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከኤቨርተን ጋር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቅቋል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ጨዋታዎች ዎልቭስ ሌስተር ሲቲን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ፉልሃም እና ሳውዝሃምፕተን ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን ጨርሰዋል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን÷ ቶተንሃም ሆትስፐር ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር ይጫወታል፡፡