በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 452 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው ፤የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7 ሺህ 294 የላቦራቶሪ ምርመራ 452 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 301፣ ከጋምቤላ ክልል 34፣ ከኦሮሚያ ክልል 19፣
ከትግራይ ክልል 32፣ ድሬደዋ 0፣ ደቡብ ክልል 17፣ ከሐረሪ ክልል 2፣ ከሲዳማ ክልል 5፣ ከአማራ ክልል 9፣ ከሶማሌ ክልል 12 እና ከአፋር ክልል 21 ናቸው።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 350 ሺህ 160 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 524 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢቢሲ ዘግቧል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎም በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅትም 38 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ሕክምና መከታታያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።
ባለፉት 24 ሰዓታት 58 ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 506 ደርሷል።