Fana: At a Speed of Life!

በሊጉ የበዓል ሰሞን መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ፤ክሪስታል ፓላስ ከአርሰናል ዛሬ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከአርሴናል ዛሬ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ።

በከፍተኛ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ወደቪላ ፓርክ ተጉዞ ከቀኑ 9:30 ላይ ከአስቶን ቪላ ጋር በሚያከናውነው ጨዋታ ከባድ ፈተና እንደሚጠብቀው ይገመታል።

በአውሮፓውያኑ የገና በዓል ሰሞን ጨዋታዎች ምሽት 12 ላይ ቀጥለው ሲካሔዱ÷ ብሬንትፎርድ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ኖቲንግሃም ፎሬስትን በሜዳው ጂቴክ ኮሚዩኒቲ የሚያስተናግድ ሲሆን ኒውካስል ዩናይትድ በበኩሉ ወደፖርትማን ሮድ ሜዳ ተጉዞ ኢፕስዊች ታውንን ይገጥማል።

በተመሳሳይ ሰዓት ዌስትሃም ዩናይትድ ከብራይተን ሆቭ አልቢዮን በለንደን ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በሌላ በኩል ምሽት 2:30 በለንደን ደርቢ ክሪስታል ፓላስ ከአርሰናል በሴልኸርስት ፓርክ የሚጫወቱ ሲሆን÷ መድፈኞቹ ከመሪው ሊቨርፑል ያላቸውን የ6 ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደሜዳ ይገባሉ ።

ሁለቱ ቡድኖች በእንግሊዝ የካራባኦ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ረቡዕ ታሕሣሥ 9 በኢሚሬትስ ስታዲየም ተጫውተው መድፈኞቹ 3 ለ 2 አሸንፈው ወደግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.