Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ ገና የንግድ ባዛርና አውደርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 አዲስ ገና የንግድ ባዛር እና አውደርዕይ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል፡፡

የንግድ ባዛር እና አውደ ርዕዩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) የከፈቱት ሲሆን÷መርሐ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ አስከ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡

በዚሁ ወቅት ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር)÷ያለፉት አምስት ወራት ኢትዮጵያ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ትግበራ ማግኘት የሚገባትን ትሩፋቶች ያገኘችበት ነበር ብለዋል፡፡

በተለይም ባለፉት ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር መገኘቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤት መሆኑንም ተናግረዋል።

የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት በተሰራው ስራ ሕግና ስርዓት አክብረው ለመስራት ፍቃደኛ ባልሆኑ ከ108 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ በንግድ ህጉ መሰረት አስተማሪ ርምጃ ተወስዷል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.