በአማራ ክልል ከ16 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት ከ16 ቢሊየን 922 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ።
በቢሮው የግብር ትምህርት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ታዘባቸው ጣሴ እንዳሉት÷ ክልሉ እስከ ኅዳር ወር አጋማሽ ድረስ ከ16 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከመደበኛና ከከተማ አገልግሎት 71 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን አንስተዋል።
ዕቅዱን ለማሳካትም የተለያዩ ስልቶች ተቀርፀው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ሲሆን÷ እስካሁን ባለው እንቅስቃሴም አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ነው የተባለው።
በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል።