Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማሳደግ እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሳዑዲ ዓረቢያ ምክትል ግብርና ሚኒስትር አሕመድ ቢን ሳሊህ ቢን አይዳህ አል ሃማሽ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያና ሳዑዲ  ዓረቢያ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በግብርና ዘርፍ በትብብርና በቅንጅት በመስራት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

አሕመድ ቢን ሳሊህ ቢን አይዳህ አል ሃማሽ በበኩላቸው÷ ሳዑዲ በኢትዮጵያ  በግሉ ዘርፍ የምታከናወናቸውን የኢንቨስትመንት ሥራዎች አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በቁም እንስሳት ንግድ፣ በማዳበሪያ ምርት ሽያጭና በሌሎች የንግድ ልውውጦች ላይ ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.