Fana: At a Speed of Life!

 ኢትዮጵያና ፓኪስታን በዲጅታል ሚዲያ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደርና ጀማል በከር ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር የዲጅታል ሚዲያ ልዩ አማካሪ ሚኒስትር ፋህድ ሃሩን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵና ፓኪስታን በዲጅታል ሚዲያ መስክ ሁሉን አቀፍ ትብብር ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ጀማል ÷ ዲጂታል ሚዲያ ሁሉን አቀፍ ለሆነ የሀገራት ግንኙነት እና ተግባቦት ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከፓኪስታን ጋር ልምዶችን ለመለዋወጥ እና የዲጂታል ሥነ-ምህዳሩን ለማሻሻል በትብር እንደሚሰራም አንስተዋል፡፡

ፋህድ ሃሩን በበኩላቸው÷ በዲጂታል ሚዲያ በመተባበር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ የዲጅታል ሚዲያ ፖሊሲ ልምድ ልውውጥ እንዲሁም የጋራ መግባባትና መደጋገፍን መፍጠር ይቻላል ብለዋል።

ፓኪስታን የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ በማዳበር ሀገራቱን እያቀራረበ በሚገኘው ዲጅታል ሚዲያ ሁሉን አይነት ድጋፍና እርዳታ እንደምታደርግ ማረጋገጣቸውንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ የዲጂታል ሚዲያ መድረኮችን በማሰስ ቀጣይነት ያለው የትብብር ማዕቀፍ ለመመስረት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.