Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረትና ፈረንሳይ አጋርነትን ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንና የፈረንሳይ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ምክክር በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትና የአውሮፓና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን-ኖኤል ባሮት እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ህብረቱና ፈረንሳይ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የሁለትዮሽ አጋርነትና የትብብር ማዕቀፎች አስመልክቶ ምክክር የሚደረግ ሲሆን፤ በባለብዝኃ ወገን ዲፕሎማሲ ያላቸው ግንኙነትም ሌላኛው የውይይቱ አጀንዳ ነው።

ምክክሩ የሁለቱን ወገኖች አጋርነት ይበልጥ ማጠናከርን ያለመ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ሰላም፣ ደኅንነት፣ ኢኮኖሚ፣ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና ትምህርት ከአፍሪካ ኅብረትና የፈረንሳይ የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.