Fana: At a Speed of Life!

የሶሪያ ጦር በአሌፖ ግዛት ጥቃት በፈፀሙ አማፂያን ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ጦር በሶሪያ ሰሜን ምዕራብ በምትገኘው አሌፖ ግዛት በተለያዩ ከተሞች የሽብር ጥቃት በፈፀሙ አማፂያን ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በውጭ ሀይሎች እንደሚደገፉ የሚነገርለላቸው እና ሃያት ታህሪር አል አልሻም የሚል ስያሜ ያላቸው አማፂ ቡድኖች ትናንት ምሽት በርካታ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡

በግዛቷ የሚገኙ መንደሮች ቀደም ሲል በሶሪያ የመንግስት ሀይሎች ቁጥጥር ስር ብትሆንም አማፂያኑ ሰርገው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸው ተነግሯል።

አማፂያኑ የሂዞባላህ የጦር ሰፈር እንደሆነ በሚነገረው የአሌፖ ግዛት 10 ኪሎ ሜትር ዘልቀው በመግባት በአል ናይራብ አየር ማረፊያ ላይም ጥቃት መፈፀማቸውም ተገልጿል፡፡

በሩሲያ እና ቱርክ አደራዳሪነት በሶሪያ መንግስት እና በአማጺያኑ መካከል የተኩስ አቁም ከተደረገበት የፈረንጆቹ 2020 በኋላ ከባድ እና መጠነ ሰፊ ጥቃት ሲፈጸም የአሁኑ የመጀመሪያ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎም ዛሬ ጠዋት የሶሪያ እና የሩሲያ ጄቶች በአማፂያን ላይ የተቀናጀ ጥቃት መፈፀማቸውን እና በታጠቂ ቡድኑ ላይ በርካታ ኪሳራ ማድረሳቸውን የሶሪያ ጦር አስታውቋል፡፡

የሩሲያ እና የሶሪያ ጄቶች በአማፂያኑ ላይ ከበባ በማድረግ የሚፈፅሙትን ጥቃት ተከትሎ ከአሌፖ ወደ ደማስቆ የሚወስደው ዋና መንገድ በጊዜያዊነት መዘጋቱን የዘገበው አል አራቢያ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.