የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በባህርዳር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የአማራ ክልል የማጠቃለያ መርሐ ግብር በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)፣ የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ መለሰ ዓለሙ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ዘርፍ ሃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተግኝተዋል፡፡
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የሀሳብ ልዕልና፣ ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡