የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በባሕርዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ በባሕርዳር የገቡ ከፍተኛ አመራሮች የከተማዋን የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)፣ የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ መለሰ ዓለሙን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በጉብኝታቸው በጣና ሐይቅ ዳር እየተገነባ የሚገኘውን የጣና ማሪና ፕሮጄክትን ተመልክተዋል።
የጣና መሪና ፕሮጀክት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን በማላበስ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ይጨምራል መባሉን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡