Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ስደተኞች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ በርካታ ስራዎችን እያከናወነች መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ስደተኞች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እና በመደበኛ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ በርካታ ስራዎችን እየሰራች መሆኗን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው 115ኛው የአለም አቀፉ ስደተኞች ካውንስል ጉባኤ ላይ በስደተኞች ደህንነት ላይ ያላትን አቋም ይፋ አድርጋለች፡፡

አምባሳደሩ የኢትዮጵያን አቋም ይፋ ባደረጉበት ወቅት÷ ሀገሪቱ የፍልሰተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ እና በመደበኛ እና ህጋዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል በርካ ስራዎች እየሰራች መሆኗ አስረድተዋል፡፡

በዚህም ከተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የሰለጠኑ ሰራተኞችን ወደ ሀገራቱ ሄደው መስራ በሚችሉበት ዙሪያ የሁለትዮሽ ስምምነት መደረጉን ለማሳያነት አንስተዋል፡፡

መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ለሀገሪቱ ተግዳሮት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል መሆናቸውም ጠቅሰዋል፡፡

በአየር ንብረት ሳቢያ ለሚፈጠሩ መፈናቀሎች አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መፍትሄ እንዲሰጥም ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.