Fana: At a Speed of Life!

ሕብረተሰቡ የባንክ ምስጢር ቁጥር በመቀበል ከግለሰቦች አካውንት ብር ከሚመዘብሩ ወንጀለኞች እንዲጠነቀቅ ፖሊስ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከባንክ እንደተደወለ አስመስለው የተለያዩ ስልኮችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ ምስጢር ቁጥር በመቀበል በማጭበርበር ከግለሰቦች አካውንት ብር ከሚመዘብሩ ወንጀለኞች ሕብረተሰቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሳሰበ፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ የባንክ ስሞችን በመጠቀም ለግለሰቦች በመደወል የባንክ አካውንቱን በመናገር ሲስተም እያስተካከልን ነው፤ የባንካችን ተሸላሚ ደንበኛ በመሆንዎ ‘እንኳን ደስ አለዎት’ በማለት እና የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም የሞባይል ባንኪግ ኮድ እንዲያስገቡ በማግባባት በአካውንት የተቀመጠ ገንዘብን ወደራሳቸው የሚወስዱ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን ደረሼበታለሁ ብሏል ፖሊስ፡፡

ሕብረተሰቡም የእንዲህ አይነት ወንጀል ሰለባ እንዳይሆን እራሱን መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝቧል።

በወንጀል ድርጊቱ በመሳተፍ ፖሊስ የጠረጠራቸውን ከዚህ በታች በስምና በፎቶ ግራፍ የተገለጹትን ተጠርጣሪዎች ህብረተሰቡ ሲመለከት የፖሊስን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.