Fana: At a Speed of Life!

ዜጎች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ተመዝጋቢ እንዲሆኑ የሐይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነዉ ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም ዜጎች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ተመዝጋቢ እንዲሆኑ የሐይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ላይ ለሀይማኖት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ዋና ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ÷ ዜጎች ስለ ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ከሐይማኖት አባቶች መረጃ አለማግኘታቸዉ እስካሁን ለማሳካት ከታሰበዉ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነዉ ብለዋል ።

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮዳሔ አርዓያሥላሴ በበኩላቸው÷ ሁሉም ዜጎች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ተመዝጋቢ እንዲሆኑ የሐይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብሩ ላይ የሐይማኖቶች አባቶች የተገኙ ሲሆን÷ የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያን የተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.