Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በኳታር አለም አቀፍ የቱሪዝም አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዶሃ ኤግዚቢሽንና ኮንቬንሽን ሴንተር እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው “ኳታር ትራቭል ማርት 2024 ” የቱሪዝም አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው።

በአውደ ርዕዩ በኳታር፣ የመን እና ኢራን የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ እና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈይሰል አሊዪ ኢብራሂም፣ በኳታር የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የኩባንያ ባለቤቶች እና ጎብኚዎች ተገኝተዋል።

በዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ጋር በመሆን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታዎች፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የኢትዮጵያ ታሪክ በአውደ ርዕዩ ለጎብኚዎች መቅረቡን በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለሶስት ቀናት የሚቆየው ይህ አውደ ርዕይ በቱሪዝም ልማት ውስጥ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለማካሄድ እድል የሚሰጥ ነው የተባለ ሲሆን÷ የቱሪዝም ባለሙያዎችም ስለ ዘርፉ የሚወያዩበት መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.