Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የፀረ ጾታዊ ጥቃት ቀን በድሬዳዋ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የፀረ ጾታዊ ጥቃት ቀን “የሴቷ ጥቃት የኔም ነው፤ ዝም አልልም” በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

በመር ሐግብሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባዔ ዛሐራ ሁመድና የድሬደዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ፈትህያ አደን ተገኝተዋል፡፡

የሴቶችን ፆታዊ ጥቃት የመከላከል ተግባር የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

”ችግሩን ለመከላከል እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ለውጥ እያመጡ ቢሆንም ከስፋቱ አንፃር አሁንም የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፉ የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚከበር የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.