አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ኮንፈረንሱ “የበለጸገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመድረኩ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር እና የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል፡፡