Fana: At a Speed of Life!

የሚዛን አማን የቡና ምርት ጥራት፣ ምርመራና ሰርተፊኬሽን ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡና ዕዝ ሰንሠለትን በመጠበቅ ምርታማነትንና ጥራትን በማሻሻል የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ አልሞ የተቋቀመው የሚዛን አማን የቡና ምርት ጥራት፣ ምርመራና ሰርተፊኬሽን ማዕከል ተመረቀ፡፡

ማዕከሉን የመረቁት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ማዕከሉ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኙና ግብይት እንዲፈጽሙ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ርዕሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ማዕከሉ የኢትዮጵያን ቡና አንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸው÷ ከዚህ በፊት ሲነሱ የነበሩ ችግሮችንም ይፈታል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ዛሬ የተመረቀው ማዕከል በክልሉ ሁለተኛ መሆኑ እና ሦስተኛ ማዕከል በቀጣይ በቴፒ ከተማ እንደሚከፈትም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.