Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 337 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የመኸር ወቅት 337 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል ሲል የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ በመኸር እርሻ ልማት ሥራ 11 ነጥብ 6 ሚሊየን ሔክታር መሬት በ68 የሰብል ዓይነቶች መሸፈኑን በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር ሙስጠፋ ሁሴን ተናግረዋል፡፡

በሰብል ከተሸፈነው ውስጥ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታሩ የስንዴ ልማት መሆኑን ገልጸው÷ ከዚህም 337 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የምርት ብክነት እዳይኖርና ምርታማነት እዲረጋገጥ  እየተሠራ ባለው ሥራ በክልሉ ያሉ 600 ኮምባይነሮች እና 5 ሺህ 900 የመሬት ማለስለሻ ትራክተሮች እገዛ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የምርጥ ዘር እጥረትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተው÷ ለአብነትም የስንዴ፣ ጤፍ፣ በቆሎ እና ባቄላ ምርጥ ዘር በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ እየለማ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው÷ ከእራስ ፍላጎት አልፎ ስንዴን ወደ ውጭ በመላክ የተገኘውን ስኬት በሰብሎች ላይም መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም በቅንጅት ለአንድ ሀገር በትጋት መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.