የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የገርዓልታ ሎጅ ግንባታ ሒደትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የገርዓልታ ሎጅ ግንባታ ሒደትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሑሴንና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ ተሳትፈዋል፡፡
ገርዓልታ ሎጅ ከአካባቢው ጋር የተጣጣመ ኢኮ-ሎጅ ሲሆን÷ ተፈጥሮ ባደለው የተራራ ሰንሰለቶች ላይ እየተገነባ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
የፕሮጀክቱ ሥራ ሲጠናቀቅ ከተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ሥፍራዎች አንዱ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎቹ በቆይታቸው በክልሉ የተጀመረውን የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ሥራ ሒደት ተዘዋውረው ይመለከታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡