26 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 መጀመሪያ ሩብ ዓመት 26 የገጠር ከተሞችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ተቋሙ 120 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 90 ሺህ 573 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉም ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 11 ነጥብ 15 ቢሊየን ብር መሰብሰብ የቻለ ሲሆን÷ ከሃይል ሽያጭ ደግሞ 8 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተጠቁሟል፡፡
ካሉት የድህረ ክፍያ ደንበኞች ውስጥ 87 ነጥብ 1 በመቶ የሚሆኑት በዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሒሳባቸውን እየከፈሉ እንደሚገኙም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡