Fana: At a Speed of Life!

ጋዜጠኞች በኦሮሚያ ክልል የሰብል ልማት እና የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስተባባሪነት የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች በአርሲ እና ባሌ ዞኖች የመኸር እርሻ ሰብል ልማትን ጨምሮ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም በአርሲ ዞን ሌሞ ቢልቢሎ ወረዳ ለአዲስ አበባ ከተማ በቀን 9 ሺህ ሊትር ወተት የሚያቀርበውን ማኅበር የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ማኅበሩ ከተመሰረተ ሦስት ወር እንደሆነው እና ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል እንዳለው ተገልጿል፡፡

የወተት ምርቱን ለማቅረብም በወረዳው 642 አርሶ አደሮች ተደራጅተው እየሠሩ ሲሆን÷ የወተት ምርቱን አቀነባብሮ ለተጠቃሚ ለማድረስ ማኅበሩ ፋብሪካ እየገነባ ነው ተብሏል፡፡

የማኅበሩ ኃላፊ ሙሉጌታ ቱፋ÷ መንግሥት የገበያ ትስስር እንዲሁም ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ደግሞ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉልን ነው ብለዋል፡፡

የወረዳው አሥተዳዳሪ ዘውዱ ታሪኩ በበኩላቸው÷ ፋብሪካው እውን ሆኖ አካባቢው በወተት ምርት እንዲታወቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር በምግብ እራስን መቻል ብሎም ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ከበደ ዴሲሳ ገልጸዋል፡፡

በሌማት ትሩፋት ሥራዎች ዜጎች የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ በቤት ውስጥ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ብሎም ለገበያ እንዲያቀርቡ እየተደረገ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.