Fana: At a Speed of Life!

አፋር ክልል ለኢንቨስተሮች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች አስላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ገለፁ፡፡

አቶ አወል ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሃብቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት÷ ጥናቶችን መነሻ በማድረግ በክልሉ የሚገኙ እምቅ ሃብቶችን ለማልማት ለሚመጡ ባለሃብቶች ተገቢውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

የመሠረተ-ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው÷ ባለሀብቶች በሀገር ውስጥ መዋዕለ-ነዋያቸውን በማፍሰስ የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

የመንግሥት ድጋፍ ኢንቨስተሮች በሀገር ውስጥ የሚገኙ ፀጋዎችን እንዲያለሙ እና ለሀገር እድገት አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ይረዳል ያሉት ደግሞ የውይይቱ ተሳፊ ባለሃብቶች ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.