Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ መጀመሩን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው÷ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት ለመግባት በእጃቸው ያለውን ትጥቅ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

የተሃድሶ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ወደ ማዕከላት ገብተው የዲጅታል ምዝገባና ማረጋገጥ፣ የሳይኮ-ሶሻልና የሲቪክ ተሃድሶ ስልጠና እንደሚወስዱ ተመላክቷል፡፡

የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማህበረሰቡ ሲመለሱ ለመሠረታዊ ፍጆታ እንዳይቸገሩ የመልሶ ማቀላቀል ክፍያ እንደሚሰጣቸውም ተጠቁሟል፡፡

ኮሚሽኑ ከሰባት ክልሎች የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማዕከላት ለማስገባት የመለየት ሥራ ማጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.