Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የቱሪዝም ቀን በኦሮሚያ ክልል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የቱሪዝም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ45ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ይከበራል።

‘’ቱሪዝም ለሰላም’’ በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ አርሲ ዞን እየተከበረ ባለው የቱሪዝም ቀን የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ጀሚላ ሲምቢሩ ተገኝተዋል፡፡

በሥነ-ስርዓቱም ለአሰላ ከተማ መዳረሻ የሚሆኑ ከተሞች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፥ ከከተሞቹ መካከል የሆነችው ዴራ ከተማ የዲልፈቃር ፓርክ ጉብኝት ተደርጎበታል።

በቀጣይም ፓርኩን የቱሪስት ፍላጎት ማሟላት በሚያስችል መልኩ እንዲያደራጅ እንደሚሰራ ተነግሯል።

በሂርፓ ሽቦ እና ሊያ ዱጉም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.