Fana: At a Speed of Life!

ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ረጅም ርቀት ሚሳኤል ወደ ሩሲያ አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ፍቃድ መሠረት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ዩክሬን ወደ ብሪያንስክ ግዛት ካስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች አምስቱ በሩሲያ ጦር የከሸፉ መሆኑን የገለው የሞስኮ መረጃ፤ የአንደኛው ሚሳኤል ፍንጣሪ በሩሲያ ጦር አቅራቢያ የእሳት አደጋ ማስከተሉን አስታውቋል።

ይህ የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የሚሳኤል ጥቃት ወደ ሩሲያ ሲወነጨፍ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ዩክሬን ሚሳኤሉን ከማስወንጨፏ አስቀድሞ ከሰዓታት በፊት የሩሲያ ፕሬዚዳነት ቭላድሚር ፑቲን ግልጽ የደህንነት ስጋት መከሰቱን በመግለጽ፤ የኒውክሌር ሚሳኤል መመሪያ እንዲቀየር ትእዛዝ አስተላልፈዋል እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን ከአሜሪካ የተሰጣትን ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ሩሲያን ለመምታት እንድትጠቀምበት ፍቃድ መስጠታቸው ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎም ዩክሬን ሚሳኤሎቹን የምትጠቀም ከሆነ ሩሲያ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ማስጠንቀቋ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.