Fana: At a Speed of Life!

የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢንተርኔት ለመላው ኢትዮጵያውያን” በሚል መሪ ሃሳብ የዘንድሮው የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡

በፎረሙ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ሀላፊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ፣ የቴክኖሎጂ ልሂቃን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ፎረሙ በበይነ መረብ ተደራሽነት፣ ዲጂታል ማካተት ላይ ያሉ ቁልፍ ተግዳሮቶችን በመለየት ግንዛቤ ለመፍጠር እና ጥር 2025 ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ኮንፈረንስ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በፎረሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን አለማየሁ (ዶ/ር)÷ኢንተርኔት የእድገት መሰረት፣ ግለሰቦችን፣ ማህበረሰቦችን እና ሀገራትን የሚያገናኝ ድልድይ ሆኗል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፕሬዚዳንት አስራት ሙላቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ኢንተርኔት የዓለም ህዝቦች እንዲተሳሰሩና አዳዲስ ነገሮችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል በመሆኑ አለምን እየቀየረ ነው ብለዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.