ኢትዮጵያ ለተመራጩ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፤ ሶማሊላንድ በቅርቡ ባካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ በመመረጣቸው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል።
የተመረጡት ፕሬዚዳንት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ እና ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ ላሳዩት ተምሳሌታዊነት ኢትዮጵያ አድናቆት እንዳላት የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ መጪው የሶማሊላንድ አስተዳደር ስኬታማ ጊዜ እንዲገጥመው ተመኝቷል።
የሶማሊላንድ ምርጫ ኮሚሽን የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።