Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2016/17 የመኸር ወቅት ከለማው ሰሊጥ 4 ሚሊየን 746 ሺህ 636 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በምርት ዘመኑ 458 ሺህ 264 ሔክታር መሬት በማልማት ከ3 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን በቢሮው የሰብል ልማት ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በተደረገው የተቀናጀ ርብርብም ከዕቅድ በላይ 593 ሺህ 329 ሔክታር ማልማት መቻሉን እና ከዚህም 4 ሚሊየን 746 ሺህ 636 ኩንታል የሰሊጥ ምርት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡

በአጠቃላይ በሰሊጥ ሰብል ከተሸፈነው ውስጥ እስከ አሁን 90 በመቶው መሰብሰቡን እና ቀሪው 10 በመቶ በመሰብሰብ ሂደት ላይ መሆኑንም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

ከዕቅድ በላይ ለመፈጸም ካስቻሉ ምክንያቶች መካከልም አንዱ በአኩሪ አተር ላይ የተፈጠረውን የገበያ ክፍተት ተከትሎ በርካታ አምራቾች ወደ ሰሊጥ ፊታቸውን ማዞራቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.