Fana: At a Speed of Life!

አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት በመሆን መመረጣቸው ተሰምቷል፡፡

የሶማሊላንድ ምርጫ ኮሚሽን የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

አብዲራህማን በምርጫው 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉት ሲሆን፥ የወቅቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ 34 ነጥብ 81 በመቶ ድምጽ በማግኘት ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በምርጫው ሂደት ውስጥ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ዋዳኒ፣ ኩልሚዬ እና ካህ ቁልፍ ተዋናዮች ሆነው መታየታቸው ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በሶማሊላንድ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን በመግለጽ ህዝቡ ላሳየው ተሳትፎ አመስግኗል።

አዲስ የተመረጡት ፕሬዚዳንት በሚቀጥሉት ቀናት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ያሳውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሙስታክባል ሚዲያ ነው የዘገበው፡፡

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባለፈው ሳምንት ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም መካሄዱ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.