Fana: At a Speed of Life!

የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ባቀድነው አቅጣጫ መሠረት በውጤታማነት እየተተገበረ ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ባቀድነው አቅጣጫ መሠረት በውጤታማነት እየተተገበረ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷የተትረፈረፈ የምግብ ምርት ለማምረትና የተመጣጠነ የምግብ ዋስትና ስርዓትን ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ የተጀመሩ ሥራዎች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የጎበኙት የደብረ ሆላንድ የዶሮና እንቁላል ምርት ማዕከልም ሀገራዊ ውጥንን ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ማዕከሉ ከ90 ሺህ በላይ እንቁላል በየቀኑ እያመረተ መሆኑ ደግሞ ለገበያ በቂ ምርት እንዲቀርብ እና በአነስተኛ ዋጋ ለተጠቃሚ እንዲደርስ ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል፡፡

የውጭ ባለብቶች በሌማት ትሩፋት ሥራ ተሰማርተው ማየታችን ኢኒሼቲቩ ለኢንቨስትመንት ምቹ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.