Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል የሂዝቦላህን ዋና ቃል አቀባይ መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የሂዝቦላህ የሚዲያ ሃላፊ የሆነውን ሞሃመድ አፊፍ ሰይድን መግደሉን አስታውቋል፡፡

የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ቤሩት እና በሰሜን ጋዛ የሚፈጽመው የአየር ጥቃት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡

ጦሩ በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ቤሩት የሂዝቦላህ ደጋፊ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ሕንጻ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

በጥቃቱም ለልዩ ስብሰባ ሕንጻው ውስጥ የነበረው የሂዝቦላህ የሚዲያ ሃላፊ ሞሃመድ አፊፍ መገደሉ ነው የተገለጸው፡፡

ሞሃመድ አፊፍ በቅርቡ በእስራኤል ጥቃት የተገደለው የቡድኑ የቀድሞ መሪ ሃሰን ነስራላህ የሚዲያ ጉዳዮች አማካሪ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

በሊባኖስ በሚዲያ ግንኙነት ጉዳዮች ዙሪያ አንቱታን ያተረፈ የቡድኑ ቁልፍ ሰው እንደነበርም ዘገባው አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ጋዛ በፈጸመው ጥቃት የ72 ዜጎች ሕይወት ማለፉን ተሰምቷል፡፡

ቤይት ላሒያ በተሰኘ ግዛት በሚገኝ ባለብዙ ፎቅ መኖሪያ ሕንጻ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ በርካታ ዜጎች መጎዳታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.