ከ120 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የቂልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከ120 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የቂልጦ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመርቋል፡፡
ሆስፒታሉን መርቀው የከፈቱት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ናቸው፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የፌደራል፣ የክልሉ ፣ የዞንና የወረዳው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና፣የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የወረዳው ነዋሪዎች መገኘታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡