የጋምቤላ ክልል መንግስት ለ138 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለ138 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ኡቶው ኡኮት እንዳሉት የክልሉ መንግስት ለታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረገው የክልሉ ይቅርታ ቦርድ ያደረገውን ማጣራት መሠረት በማድረግ ነው።
በመሆኑም ዛሬ ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የበደሉትን ህዝብና መንግስት ለማካካስ ዝግጁ መሆናቸውና በፈጸሙት ድርጊት መፀፀታቸው የተረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዶል ኡኩሪ ÷ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች 138 መሆናቸውን ጠቅሰው እነዚህም በክልሉ አራት ማረሚያ ቤቶች የነበሩ እንደሆነ ገልጸዋል።
በይቅርታ ከተለቀቁት የህግ ታራሚዎች መካከል ሶስቱ ሴቶች መሆናቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ይቅርታው በ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ወቅት ሊደረግ ታስቦ በተለያዩ ምክንያት መዘግየቱ ተመላክቷል፡፡