Fana: At a Speed of Life!

ፌዴራል ፖሊስና የቻይና ሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የቻይና ሕዝብ ደኅንነት ምክትል ሚኒስትር ዢ ያንጁን በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በቅንጅት ለመሥራት ስምምነት በደረሱባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ድንበር ተሻጋሪ ወንጀልን በመከላከል፣ በተፈላጊ ወንጀለኞች ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ እና ግብዓት ድጋፎች አመርቂ ውጤት መገኘቱም በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የተጠናከረና ቅንጅታዊ ትብብርን ለማስቀጠልም የኢትዮ-ቻይና የሕግ አስከባሪ ትብብር ማዕከል በአዲስ አበባ በማቋቋም እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በሁለቱ ተቋማት የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን እና የቤጂንግ ማኒሲፖል የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ የመግባቢያ ስምምነት ፈርመዋል፡፡

በዚህም በልምድ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.