Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛን አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሪሎ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲቋጭ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና በሱዳን ጦር መካክል የተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት 1 ዓመት ከ7 ወር ያስቆጠረ ሲሆን በተለያዩ ሀገራት በፖለቲካዊ ድርድር ግጭቱን ለማድረግ ሙከራዎች ቢደረጉም እስካሁን እልባት አላገኘም።

በተመሳሳይ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጃፓን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት አምባሳድር ሺሚዙ ሺንሱኬ ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ከጃፓን መንግስት ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው በበኩላቸው በሱዳን ያለው የእረስ በርስ ጦርነትን ለመቋጨት የአፍሪከ ህብረት እና ኢጋድ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማምጣት ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በለሎች ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.