እውን በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የጅምላ አፈሳ እየተፈጸመ ነውን?
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ከሰሞኑ የጅምላ አፈሳ ድርጊት እየተፈጸመ ነው የሚሉ መረጃዎች በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲሰራጩ ይስተዋላል፡፡
የጅምላ አፈሳው በተለይ በወጣቶች እና በቀን ሥራ በተሰማሩ ዜጎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን እንዲሁም ከታፈሱ በኋላ በትምህርት ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ውስጥ እንዲቆዩ እንደሚደረግ ይነገራል፡፡
በቀጣይም የታፈሱ ዜጎችን ለመፍታት በየአካባቢዎቹ የሚገኙ ሚሊሻዎች የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚጠይቁ ይጠቀሳል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እውን የጅምላ አፈሳ ድርጊት እየተፈጸመ ነው በሚል በኦሮሚያ ክልል ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርቧል፡፡
የጅምላ አፈሳ አለ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ስለመሆኑና ሌሎች የክልሉ አሁናዊ የጸጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ከክልሉ ያገኘነውን ዝርዝር ምላሽ የምናቀርብ ይሆናል፤ ይጠብቁን …
በመላኩ ገድፍ