ምክክር ኮሚሽኑ ከመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከ56 የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት÷ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስልጠና እና ግብአት በመስጠት ለኮሚሽኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል።
በ11 ክልሎች ውስጥ 15 የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተከፈቱት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ኮሚሽኑ እስካሁን ድረስ ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።
በውይይቱ ከ1 ሺህ 200 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንት እና ተወካዮች እየተሳተፉ መሆኑ ታውቋል።
በአልማዝ መኮንን