Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ እና የቻይና ፕሬዚዳንቶች ፔሩ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና አቻቸው ሺ ዢንፒንግ በእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚክ ትብብር ጉባዔ ለመሳተፍ ፔሩ ሊማ ገቡ፡፡

ፕሬዚዳንቶቹ ሊማ ሲደርሱ በፔሩ አቻቸው ዲና ቦሉአርቴ  ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል፡፡

በስልጣን ዘመን የመሪዎቹ በሊማ መገናኘት የዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጥን ተከትሎ የመጨረሻቸው ሳይሆን እንደማይቀርም ተነግሯል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን እና ሺ ከእስያ ፓስፊክ ጉባዔ ጎን ለጎን ነገ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ጉባዔው በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በማተኮር አካታች ኢኮኖሚን መገንባት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ይመክራል መባሉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

የእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር 60 በመቶ የዓለም ኢኮኖሚን የተቆጣጣሩ እና 40 በመቶ የዓለም ንግድን የያዙ 21 ሀገራትን ያሰባሰበ ተቋም ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.