ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በአብአላ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኪልበቲ ረሱ አብአላ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝት መርሐ ግብሩ በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን አሊሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን የክልሉ ሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡