ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ላቦራቶሪ ዕቃዎች ተበረከተለት
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ዣንገባኦ ሁዋን ግሩፕ በርካታ የፎረንሲክ ላቦራቶሪ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አበርክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በድጋፍ የተበረከቱ ዕቃዎችን የተረከቡ ሲሆን ኩባንያው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ኮንግ ዚንሚንግ በበኩላቸው÷ ሰላምና ደህንነት የአንድ ሀገር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ጉዳይ በመሆኑ ይህን ድጋፍ በማድረጋችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
በቀጣይም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በወንጀል መከላከልና በምርመራ ዘርፍ ለሚሰራው ስራ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡