በዕጣና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ ከምን ደረሰ?
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በዕጣና በጨረታ ቢተላለፉም ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና ንግድ ቤቶች “ለሕገ-ወጥ ድርጊት እየዋሉ ነው” የሚል ቅሬታ እየቀረበ ነው፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጉዳዩ ላይ ባደረገው ማጣራት÷ በዕጣ እና በጨረታ የጋራ ቤቶች የደረሳቸው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።
በዚህ መሰረት የተወሰኑት ወደቤታቸው የገቡ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ የቤት ዕድሳት ሥራ በማከናወን ላይ መሆናቸውን ያገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
ወደ ቤታቸው ለመግባት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ያላደረጉ እንዲሁም ቤት ለማደስ የጊዜ እጥረት ያጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች እስከ ሕዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ይሁን እንጂ አሁንም በርካታ ቤቶች ለታለመላቸው ዓላማ ሳይውሉ ለቆሻሻ መጣያ፣ ለእንስሳት መዋያና ማዳሪያ እንዲሁም ለሕገ-ወጥ ተግባር እየወሉ እንደሆነ የሚገልጹ መረጃዎች በአንዳንድ አካላት እና በማኅበራዊ ሚዲያ ሲስተጋባ ይስተዋላል፡፡
በጉዳዩ ላይ የሚመለከተውን አካል አነጋግረን የቤቶቹ ጉዳይ ከምን እንደደረሰና ቀጣይ እርምጃ ምን እንደሚሆን ምላሹን እናቀርባል፤ ይጠብቁን!!
በዮሐንስ ደርበው