Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ምክክር አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከናሚቢያ፣ ጊኒ፣ አንጎላ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻዎቻቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ውይይቱን ያደረጉት ከናሚቢያ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር ፔያ ሙሽሌንጋ፣ ከጊኒ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሞሪሳንዳ ኩያቴ፣ ከአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴቴ አንቶኒዮ እንዲሁም ከዲሞክራክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴሬሴ ካይክዋምባ ዋግነር ጋር ነው፡፡

በምክራቸውም በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ውይይቶቹ የተካሄዱት በሩሲያ-ሶቺ እየተካሄደ ከሚገኘው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የመጀመሪያ የሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.