ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዑጋንዳ እና ርዋንዳ አቻዎቻቸው ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዑጋንዳ እና ርዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከዑጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄነራል ኦዶንጎ ጄጄ አቡበከር እና ከርዋንዳው አቻቸው ኦሊቨር ጄፒ ንዱሁንግሪ ጋር ባደረጉት ጋር ውይይት÷ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ከውይይታቸው በኋላም ሀገራቱ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ውይይቶቹ የተካሄዱት በሩሲያ ሶቺ እየተካሄደ ከሚገኘው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የመጀመሪያ የሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን መሆኑ ተገልጿል፡፡