ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ።
ከመጀመሪያው የሩሲያ አፍሪካ የሚኒስትሮች አጋርነት ፎረም ጎን ለጎን የተወያዩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ፤ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል።
በዚህም የጋራ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ በሚያስችሉ የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት መክረው፤ ትብብርን ለማጠናከር እና ያለውን ኢኮኖሚያዊ አቅምን አሟጦ ለመጠቀም ከስምምነት መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።