Fana: At a Speed of Life!

ለህዝቦች አብሮነትና ገፅታ ግንባታ የሶስት ወራት የንቅናቄ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለህዝቦች አብሮነትና ገፅታ ግንባታ የሶስት ወራት የንቅናቄ መርሐ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡

ንቅናቄው ከሕዳር 7- የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ክልሎች፣ የፌዴራል ተቋማትና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

ንቅናቄው በባህል፣ ኪነ ጥበብና ስነ ጥበብ ዘርፍ ያለውን ሁለንተናዊ ሀገራዊ ጠቀሜታ ማሳድግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ የምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች የባህልና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡

ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን የኪነ ጥበብ  ኢንዱስትሪ ያሳድጋል የተባ ሲሆን በፌስቲቫሉ ባህልና ኪነ ጥበብን በማስተዋወቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ እውቅና እንደሚሰጥም ተመላክቷል፡፡

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.