የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት ሪፎርም መጀመራችን ይታወቃል ብለዋል።
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር አብይ ኮሚቴ ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄዱን ገልጸው፤ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎችንም ጎብኝተናል ሲሉ ገልጸዋል።
የመጀመሪያው ዙር የቀዳሚ ምዕራፍ ሥራዎቻችንን በዚህ ምዕራፍ የተካተቱ ስምንት ተቋማት በተገኙበት ገምግመናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በቀጣይም መልካም ጅምሮችን አጠናክሮ በማስቀጠል በሪፎርሙ የታቀፉ ተቋማት ያላቸውን ልምዶች የሚቀያየሩበት አውድ መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
ተቋማት ያከናወኗቸውን ተግባራት በዝርዝር በመቃኘት ጥንካሬዎችን፣ ውስንነቶችና በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይም አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡