Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ የድንበር አስተዳዳሪዎችና ኮሚሽነሮች የጋራ ስብሰባ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀን ሲካሄድ የነበረው 28ኛው የጋራ የድንበር ኮሚሽን ስብሰባ የጋራ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት በማድረግ ተጠናቋል።

የስብሰባው ልዑክ መሪ የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፤ በስብሰባው ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት መደረጉን ገልጸዋል።

የጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ጸሐፊ ሱሉማን ሙአሚን በበኩላቸው፤ ይህ ስብሰባ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ጥልቅ ውይይት አድርጓል ብለዋል።

በምጣኔ ሀብትና ፖለቲካ እንዲሁም በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች የትብብር መስኮችን የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.